Skip to Content

መጋቢ ሄኖክ አለማየሁ

13 ኦገስት 2024
Squadwerk Innovations Pty Ltd
| No comments yet

Listen audio

ስሜ ሄኖክ አለማየሁ ይባላል። የአንዲት ሚስት ባል እና የ3 ልጆች አባት ነኝ። ተወልዬ ያደግኩት አዲስ አበባ ሲሆን ጌታን መከተል የጀመርኩት በፈረንጆች አቆጣጠር 1998 ነበር። በወቅቱ የኦርቶዶክስ ተሃድሶ እንቅስቃሴ በሀይለኛ ሁኔታ በምድሪቷ ላይ የተነሳበት ወቅት ነበር። እና የኔም የመዳን እና ወደ ጌታ መምጫ መንገድ ይህ እንቅስቃሴ ነበር። ታሪኩ እንዲህ ነበር። ከእኔ በፊት በዛ እንቅስቃሴ ወደ ጌታ የመጣች አሁን በሜኔሶታ የምትኖር እኅት ወንጌልን ነግራ ወደ ቤተክርስቲያን ጋበዘችኝ። . 

የመጀመሪያ ተጋብዤ የሄድኩበት ቦታ የካህናት ሚካኤል ሰንበት ትምህርት ላይ ነበር። የእግዚአብሔር መለኮታዊ ጥሪ ወደ ህይወቴ የመጣበትን ስፍራ እና ቀን ለዘላለም በማልረሳው ሁኔታ በውስጤ የታተመበት ስብከቱ። ሰባኪው ውስጤ የተፈጠረው ስሜት አሁን ድረስ ትኩስ ሆኖ በውስጤ አለ። የዛን ቀን በህይወቴ ጌታን ለመከተል የወሰንኩበት። እና ህይወትን ከዛ በፊት አይቼ በማላቅበት ሁኔታ ማየት የጀመርኩበት ነበር። እንዳሁኑም ጌታን የምትቀበሉት ተብዬ ሳይሆን የወሰንኩት ለራሴ በውስጤ የወሰንኩት ውሳኔ ነበር። በዛ ስፍራ የጀመረው መንፈሳዊ ጉዞዬ በጣም በአስደሳች ሁኔታ ቀጠለ። 

As it happened, my acceptance of the Lord wasn't a suggestion from others but a decision I made within myself. On that day, the sermon title was "Lazarus Will Rise." When I went to that place, it was a time in my life when all hope had been cut off. The life I was living in the world had overwhelmed me, and I was confused about what to do next and how to continue living. Everything seemed dark at that time. A young man named Abush, who was around my age, began the sermon by saying, "The title of my sermon is 'Lazarus Will Rise.'" He continued by recounting the story of Lazarus, the brother loved by Martha and Mary, who was buried and had been dead for four days when Jesus arrived at Martha and Mary's house. He explained how Jesus raised Lazarus from the dead and gave him life again. As he was speaking, it felt as though he was narrating my life story. For the first time, my soul heard the voice of its Creator, and as the Holy Spirit was speaking through that brother, I felt a great light shine within me. I was filled with hope, thinking, "I will not die; there is another kind of life on this earth." I made a decision to continue my life with this Lord. I was filled with incredible joy. Though nothing around me had changed, I was transformed forever. I left that Sunday school class, feeling touched in both place and time. My spiritual journey, which began in that place, continued in a very joyful way.

ብዙም ሳይቆይ የተሃድሶ እንቅስቃሴ በየስፍራው ኦርቶዶክስ ቸርቿች ውስጥ ታገደ። ስለሆነም በየአካባቢው አዳራሽ በመከራየት፣ ገሚሱም በሰዎች ግቢ ውስጥ የላስቲክ ዳስ በመስራት እንቅስቃሴው ቀጠለ። እኔም በመገናኛ አካባቢ በወገኖች ግቢ ውስጥ የቀጠለውን ህብረት ተቀላቀልኩ። በህይወቴ የማልረሳው የጌታ ፍቅር፣ የቅዱሳን ፍቅር፣ የቃሉ ፍቅር፣ የፀሎት ፍቅር ያየሁበት፣ የተለመደሁበት ወቅት ነበር። ዛሬ ላለሁበት ህይወት እና አገልግሎት ትልቁ መሰረት ይህ እንቅስቃሴ እና ህብረት ነው። ጌታን እንድወድ፣ ቃሉን እንድንወድ ያረገኝ ያደኩበት የኦርቶዶክስ ተሃድሶ ህብረት ነው። ከጌታ ጋር በነበረን ጥሩ ህብረት ብዙም ሳንቆይ ብዙዎቻችን ወደ አገልግሎት ገባን። በውስጣችን የነበረው ንፁህ የጌታ ፍቅር ለእርሱ እንድንሮጥ አቅም ስለሆነን፣ ብዙዎች በምስክርነታችን ወደ ጌታ መጥተዋል። ከቤተሰቤ ጀምሮ ብዙዎችን ጌታ አውርሶኛል። እግዚአብሔር በዛ ህብረት አስታጥቆናል። አሳድጎናል። 

እኔ እና አንድ ወንድም ስለ ቀጣይ ህይወታችን ብዙ ጊዜ አንመካከር ነበር። እና እስከ መቼ ከቤተሰብ ጋር ሸክም ሆነን እኖራለን፣ ስራ የለንም፣ በዚህ ሁኔታ ከቀጠልን ቤተሰብ መመስረት አንችልም። እድሜያችንም ይሄዳል፣ ምን ማረግ አለብን እንያልን፣ ማንም ወጣት ስለ ነገው እንደሚያስብ እና እንደሚወያይ እንወያይ ነበር። በዚህ አሳብ ውስጥ እያለን፣ ሳውዝ አፍሪካ የስራ እድል እንዳለ ሰዎች ሄደው እራሳቸውን ችለው፣ ጥሩ ኑሮ እንደምኖሩ እና ከሰፈራችን ከእኛ በፊት የሄዱ 2 ልጆች ያሉበትን ሁኔታ ሰማን። እኛም በሰማነው ዜና ለመሄድ ወሰንን፣ ሁለታችንም እዛ ምድር ላይ የነበረን ነገር እንዳለቀ በውስጣችን እርግጠኞች ሆንን፣ ነገሩች ተመቻችተውልን ጉዞ ወደ ሳውዝ አፍሪካ ጀመርን። ከኢትዮጵያ ኬንያ፣ ከኬንያ ታንዛኒያ፣ ከታንዛኒያ ሞዛምቢክ፣ ከሞዛምቢክ ስዋዚላንድ፣ ከስዋዚላንድ ሳውዝ አፍሪካ፣ አስራ አንድ ቀን ተጉዘን ሳውዝ አፍሪካ ገባን። 

አዲስ ህይወት ተጀመረ። ለመጀመርያ ጊዜ ከቤተሰብ ተለይተን እራሳችንን ማስተዳደር የጀመርንበት ወቅት ነበር። በእውነት የእግዚአብሔር አብሮነት ከእኛ ጋር ነበር። በጣም ደስ የሚል ጊዜ ነበር። ቤተክርስቲያን እንሄዳለን፣ ስራ እንሰራለን። ብዙም ሳይቆይ የአገልግሎት በር ተከፍቶልኝ ማገልገል ጀመርኩ። ኢትዮጵያ የነበረኝ ጊዜ የዝግጅት እንደነበረ የገባኝ ያኔ ነበር። እግዚአብሔር ኤልያስን የምትሄድበት መንገድ ሩቅ ነው፣ እና ተነስ እና ብላ አለው። ለእኔም እንደዛ ነበር። ኢትዮጵያ የምበላበት፣ የምታጠቅበት፣ የምዘጋጅበት ሰፊ ጊዜ ነበረኝ። በመቀጠልም በአገልግሎት እና በንግድ ከቆየሁ በኋላ በ2002 በሳውዝ አፍሪካ ከዛሬዋ ሚስቴ ከጄሪ እጮኝዬን ጋር ተዋወቅን። 

በ2003 ኖቬምበር 23 እግዚአብሔር በር ከፍቶልን አብረን ወደ አውስትራልያ መጣን። በሜልበርን በምትገኝው የፅዬን ቤተክርስቲያን ህብረት አረግን። በ2004 በዛው ቤተክርስቲያን ተጋባን። ጌታን በዛው ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር በኋላም በሽማግሌነት ማገልግሌን ቀጠልኩ። በ2006 ኖቬምበር 15 የመጀመርያ ልጃችን ንፍታሌም ተወለደ። በ2008 ሁለተኛ ልጃችን ሜርሲ ተወለደች። በ2014 ሶስተኛዋ ልጃችን ግሬስ ተወለደች። እግዚአብሔር የተባረከች፣ የጌታ ልብ ያላት ልጆቿን በትጋት የምታሳድግ፣ በስራ ታታሪ ሚስት ስለሰጠኝ፣ የህይወቴ እና የአገልግሎቴ ጥንካሪ የሚባለው ሁሉ ከጌታ ቀጥሎ ከጌታ የተሰጠችኝ ሚስቴ ጄሪ ናት። 

በ2008 ዓ.ም፣ የእግዚአብሔርን ምሪት በማስተዋል በጣም ጥቂት ከሆኑ ሰዎች ጋር በተለያየ ስፍራ በመገናኝት የእግዚአብሔርን ቃል መወያየት ቀጠልን። በካፌ፣ በሾፒንግ ሴንተር በኋላ፣ በኋላ የተለያዩ ቅዱሳን ቤት እያልን ህብረቱ እያደገ መጥቶ ወደ አዳራሽ ወጣ።

በ2009 ዓ.ም፣ ላይ ኦፊሻሊ የእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ተመሠረተ። በአመቱ ከቸርቿ ምስረታ ጀምሮ የነበሩ ዋና ዋና ሰዎች ተሰብስበው የእግዚአብሔርን ቃል ባንተ ተመግበናል። ህዝቡን እያወጣህ እና እያስገባህ ያለህ አንተ ነህ። ስለዚህ በተግባር መጋቢነትን በአንተ አይተናል። ስለዚህ በላያችን ላይ መጋቢ ሆነህ እንድትሾም ተስማምተናል በማለት፣ አንድ እሁድ ማለዳ ማሪብሮንግ በሚገኝ ሪስቶራንት ውስጥ በነበረን ስብሰባ ተወሰነ። ከጥቂት ወራት በኋላ የቤተክርስቲያን አንደኛ አመት በአል ላይ መጋቢ ተደርጌ ተሾምኩ። 

ከዛም እግዚአብሔር በማለዳ በውስጤ ያስቀመጠው ሰውን ለክርስቶስ ሙሉ የማረግ ራዕይ፣ በኢትዮጵያ፣ በሳውዝ አፍሪካ፣ በአውስትራሊያም በነበርኩባቸው ቸርቾች፣ በአገልግሎቴ ዘመኔ ሸክም ሆኖብኝ ስሰራው የቆየኝ ሲሆን፣ ዮሴፍ ያየው ራዕይ ፍፁሜ ያገኘው ከወንድሞቹ ርቆ በነበረበት ጊዜ እንደሆነ፣ እኔም በምክንያት ከወንድሞቼ ራቅ አድርጎ፣ ከዛ ስፍራ ሲያወጣኝ በውስጤ እግዚአብሔር ያስቀመጠውን ራዕይ ለመስራት ነፃነት እና ምቹ ሁኔታ ያገኘሁበት እድል ተፈጠረ። በእንባቆም መጽሐፍ ር፣ በፅላት ላይ በግልጽ ፃፈው እንደሚል፣ የቤተክርስቲያን ራዕይ በግልጽ በማስቀመጥ፣ አገልግሎቴን ቀጠልኩ። 

እንሆ፣ በጌታ ፀጋ ይህን አገልግሎት መምራት ከጀመርኩ 15ኛ አመት ሆነ። “ቸርነት እና ምህረትህ በህይወቴ ዘመን ይከተሉኝል። በእግዚአብሔር ቤት ለዘላለም እኖራለሁ” አሜን።

Share this post
Tags
Archive
Sign in to leave a comment